የወልዋሎ አዲግራት የእግር ኳስ ቡድን ወንጀል የስርአቱ የፖለቲካ ፖሊሲና ማናለብኝነት የወለደው ችግር ነው ።

የወልዋሎ አዲግራት የእግር ኳስ ቡድን ወንጀል የስርአቱ የፖለቲካ ፖሊሲ የወለደው ችግር ነው ። ክለቡ የወሰደው እርምጃ የበለጠ አሳፋሪ ነው ። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ብዙዎቻችን በስታዲዮሞቻችን አከባቢ የሚከሰቱ የዲሲፕሊን ግድፈቶችና የስፖርታዊ ጨዋነት መንሸዋረሮች በስፖርታዊ ሕግና ስነ ምግባር ልንለካቸው እንሞክራለን ፤ ልኬታችን ጥሩ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እግር ኳስ ግን በዘርና በማናለብኝነት ላይ ስለተመሰረተ ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት ሳይሆን ስለ ዘር ፖለቲካዊ የበላይነት የሚደከምበትና ወንጀልን የጋበዘ አደገኛ አካሔድ ነው ፤ ሁለት አማራጮች አሉ እግር ኳሱን ሰላም ለማድረግ ፤ አንድ እግር ኳስን ከነአካቴው ማገድ ወይም በዘር ላይ የተሞረኮዙ የስፖርት ቡድኖችን ማፍረስ ።

የወልዋሎ ክለብ የሰጠው አስቂኝ እና አሳፋሪ መግለጫ ዳኛውን የቡድን መሪውና ተጫዋቾች ከበው በእርግጫና በቡጢ መደብደባቸውን የካደ ነው ።

ቡጢውንና እርግጫውን በመደበቅ ዳኛው ላይ ከበባ ለፈፀሙት ተጨዋቾች በማስጠንቀቂያ አለፍኳቸው ሲል የክለቡ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ማሩ ገ/ፃዲቅ ከክለቡ ማባረሩን አሳውቋል። አሳፋሪ መግለጫ ።

የወልዋሎ ወንጀል የተፈጠረው በስልጠን ላይ ያለው አካልን መመኪያ በማድረግ ነው ።

ወልዋሉ የሰራው ወንጀል አፀያፊ ነው ።

ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ትልቅ አደጋ ከመሆኑም በላይ በሕዝቦች መካከል ጥላቻን ለመዝራት ሕወሓት ከሚተገብራቸው እኩይ ስራዎች አንዱ አካል ነው ፤ ለዚህም ሌላው ማሳያ ተጫዋቾቹ ዳኛውን ሲደበድቡ ክለቡ በገፁ ላይ ዳኛውን እያነጋገሩ ነው በማለት ወንጀሉን ሲሸፋፍን ነበር ።

እጅግ ያሳፍራል ። ይህ የፖለቲካ ስርአቱ የፈጠረው ማናለብኝነት በጊዜ መላ ሊባል ይገባል ።

የስፖርት ጋዜጠኛው መንሱር አብዱልቀኒ እንደፃፈው ይህ ስፖርታዊ ጥፋት አይደለም። ንፁህ ወንጀል እንጂ።

ዛሬ በመከላከያና በወልዋሎ ጨዋታ ላይ የታየው አሳፋሪ ጥፋት በፌዴሬሽኑ ቅጣት ብቻ መታለፍ የለበትም። አርቢትሩን የደበደቡት የወልዋሎ የቡድን መሪ በተሻሻለውና በ1997 በወጣው አዲሱ የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 541 ወይም 556 መሰረት መጠየቅ አለባቸው።

ይህ የእግር ኳስ ሜዳ ቢሆንም በአርቢትሩ ላይ የተፈፀመው ከስፖርታዊ ጥፋትም በላይ መሆኑ ተጢኖ በወንጀል ተጠያቂ መሆን እንደሚገባቸው የህግ ባለሙያዎችም የሚስማሙበት ሆኗል።

ፌዴሬሽኑ በጨዋታው ላይ በታዩ ጥፋተኞች ላይ በዲሲፕሊን ደንቡ መሰረት ፍትሐዊ ውሳኔ ማሳለፍ እንዳለበት ሁሉ የዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር ረቡዕ በኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ በሚያደርገው ጉባዔ ላይ ጉዳዩን በዚህ መልክም በመመልከት ጥፋተኛው በህግ ፊት ቀርቦ እንዲዳኝ ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ አለበት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *