የማህበራዊ ሚዲያ ማዝወተር የማስታዎስ ችሎታን ይቀንሳል- ጥናት

በዓለፉት አስስርት ዓመታት የእስማርት ስልክ ቴክኖሎጂ መስፋፋት የማህበራዊ ሚዲያ በሰፊው ለመጠቀም እድል ፈጥሯል።

በዚህም ደንበኞቹ በእየቀኑ በኢንታግራም እና የፌስ ቡክ ማህበራዊ ድረ ገጾች 70 ሚሊየን አዳዲስ ፎቶዎችና 5 ቢሊየን መረጃጀዎችን መጋራት እንደቻሉ ነው ጥናቶች የሚያረጋግጡት።

ይሁን እንጂ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎቹ የየቀኑ እለታዊ እንቅስቃሴዎቻቸውን በማህበራዊ ድረ ገጾች መጋራታቸው በህይዎታቸው ትልቅ ትርጉም የሚሰጡ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ እንቅፋት እነደሆነ ነው ጥናቱ ያረጋገጠው።

አርሻያ ቫሃብዛደህ በማሰቹሴት አጠቃላይ ሆስፒታል የአዕምሮ ሳይንስ ክፍል ዋና ስራ አስኪያጅ ሰዎች ለበርካታ ተግባራት በአንድ ጊዜ የመጋለጥ እድል ሲኖራቸው የማስታወስ ትኩረታቸው የሚበታተን መሆኑን ተናግረዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎቹ ሃሽ ታግ በማድረግ፣ መረጃዎችን በማስዋብ፣ ቀጥታ ስርጭት በማስተላለፍ ሌላ ስራ ሊሰሩብት የሚችሉበትን ጊዜና አቅም እንደሚያበክኑም ነው የገለጹት።

በዚህም ተጠቃሚዎቹ ፎቶዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ከመቀባበል በተጨማሪም ሌሎች ለህይወታቸው መሰረታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ጊዜአቸውን እንደሚያባክኑም ነው በዘገባው የተገለጸው።

በኒውሀምሻየር ኮሌጅ የስነ አዕምሮና የጭንቅላት ሳይንስት ትምህርት ክፍል የሆኑት የጥናቱ ተባበሪ ጸሀፊ ኢማ ተንፐልተንና የጥናቱ ተሳታፊዎች ግማሽ ሰዓት በወሰደ ጊዜ ቤተ ክርስትያን ላይ ጉብኝት ባደረጉ ተሳታፊዎች ላይ የዳሰሳ ጥናት አድርገዋል።

በዚህ የዳሰሳ ጥናት የመጀመሪያዎቹ 130 ተጠኚዎች በጉብኚቱ በተናጠል እራሰቸውን እንዲመሩ የተደረገ ሲሆን፥ 240 ሰዎች የያዘው 2ኛው ቡድን በዚሁ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሁለት በመሆን ተመሳሳይ ጉብኝት እንዲያደረጉ ተደርጓል።

ከተጠኚዎቹ መካከል፣ የማስታዎሻ ግላዊ ፎቶ፣ በማህበራዊ ድረገጽ የሚጫኑ ፎቶወችን የሚወስዱ እና ምንም ፎቶ ያልወሰዱ ተጠኝዎች እንደነበሩ አጥኚዎቹ ተናግረዋል።

ወዲያውኑ ጉብኚቱ እንደተጠናቀቀ፣ በሳምንቱ እና ከሁለት ሳምንት በኋላ ለተጠኝዎቹ ጉብኝታቸውን የተመለከቱ ጥያቄዎቹ ቀርበውላቸዋል።

ተጠኚዎቹ ለጥያቄዎቹ ሲቀርቡ ፎቶወቻቸውን ወይንም የማስታወሻ ደብተሮቻቸውን እንዳይጠቀሙ መደረጉን ተመራማሪዎቹ አስረድተዋል።

በዚህም ጉብኝቱን በተናጠል ያደረጉና ፎቶዎችን ለመውሰድ ያልተሳተፉ ተጠኚዎች የጉብኚቱን መሰረታዊ ጉዳዮችን የተሻለ ማስታወስ የቻሉ ሲሆን፥ ለማስታዎሻም ይሁን

ለማህበራዊ ሚዲያ ግባት ፎቶዎችን ሲሰበስቡ የነበሩ ተጠኚዎች የማስታወስ ችሎታ ዝቅተኛ እንደሆነም ነው በዘገባው የተገለጸው።

እንደ አጥኚዎቹ ሃሳብ ፎቶዎች ነገሮችን በቀላሉ ለማስታዎስ የሚያግዙ ቢሆንም ለተለያዩ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተን በምንከታተልበት ጊዜ ፎተዎችን ማንሳት የማስታወስ አቅም እንዲቀነስ ያደረጋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *