ነጭ ሽንኩርት የካንሰር፣ የልብና የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ አረጋግጠናል-ተመራማሪዎች

ነጭ ሽንኩርት ለብዙ ሺህ ዓመታት የተለያዩ በሽታዎችን ለማከም እና ለመከላከል ጥቅም ላይ ሲውል መቆየቱ ይታወቃል።

ነጭ ሽንኩርት በተፋጥሮ የያዘው አንቲባዮቲክ ንጥረ ነገር በሽታ የመከላከል አቅምን እንደሚያጎለብትም ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ጥናቶች አረጋግጠዋል።

ነጭ ሽንኩርት እንደ ፖታሲየም፣ ሴሊኒየም፣ ካልሲየም፣ ማግኒዚየም፣ ሲልከን፣ ሰልፈሪክ እና ፎስፈሪክ አሲድ፣ቫይታሚን ቢ ፣ሲ፣ ዲን በተለያየ መጠን ሲይዝ፥ ጠቃሚ ዘይቶችንም በተፈጥሮ በውስጡ አካቷል።

ነጭ ሽንኩርት በአጠቃላይ ከ400 በላይ ጠቃሚ የማዕድን ይዘቶችን በውስጡ ይዞ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ተመራማሪዎች ከሰሞኑ ባወጡት የጥናት ውጤታቸው ደግሞ ነጭ ሽንኩርትን መመገብ ለጤናችን ጠቃሚ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል።

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለፃ ነጭ ሽንኩርትን አዘውትሮ መመገብ የካንሰር፣ የልብ ህመም እና ለሁለተኛ አይነት የስኳር በሽታ የመጋለጥ አደልን ይቀንሳል።

በእንግሊዝ ኖቲንግሃም ዩኒቨርሲቲ የተሰራው የተሰራው ጥናቱ፥ ከዚህ ቀደም ነጭ ሽንኩርት ለጤና በሚሰጠው ጠቀሜታ ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶችን በዝርዝር ተመልክቷል።

የጥናት ቡድኑ መሪ ዶክተር ፒተር ሮዝ፥ ከዚህ ቀደም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶችን እንድ ላይ በመደባለቅ ዳግም ጥናት የተካሄደው ነጭ ሽምኩርት በውስጡ በርካታ ንጥረነገሮችን የያዘ በመሆኑ ነው ይላሉ።

ይህ ደግሞ ነጭ ሽንኩርት ለሰው ልጅ ጤና ምን አይነት ጠቀሜታ አለው የሚለው ላይ የተለያዩ ውጤቶች እንዲገኙ አደርጓል።

ሆኖም ግን የጥናት ቡድኑ አዲስ ባገኘው ውጤት መሰረት ነጭ ሽንኩርት የደም ግፊት መጠንን ለመቆጣጠር እንደሚረዳ እና ፀረ ካንሰር የሆኑ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ የያዘ መሆኑን ለይተዋል።

በተጨማሪም ከስኳር በሽታ ጋር በተያያዘም ነጭ ሽንኩርት በደማችን ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር እንደሚረዳ ነው ተመራማሪዎቹ የገለፁት።

ተጨማሪ የነጭ ሽንኩርት ጠቀሜታዎች

የተለያዩ ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎቻችን ተፈጥራዊ ተግባራቸውን ያለእክል እንዲያከናውኑ ያግዛል።

የሰውነት ድርቀት እንዳይከሰት እና የምግብ መፈጨት ሂደት የተሳለጠ እንዲሆንም ይረዳል።

የአተነፋፈስ ችግር ላለባቸው ነጭ ሽንኩርትን ማዘውተር የሚመከር ሲሆን፥ ጎጂ የኮሌስትሮል መጠንንም በእጅቁ እንዲቀንስ ያስችላል።

ነጭ ሽንኩርት የነርቭ ስርዓት ሂደትን በማስተካከልም ወደር የለውም።

ነጭ ሽንኩርት ግሊዮብላስቶማ የተሰኘውን እና በአንጎላችን ውስጥ ሊከሰት የሚችል ዕጢን ያስወግዳል።

ነጭ ሽንኩርት ለጉንፋን፣ በተለምዶ የብርድ በሽታ ለምንለው እና ለሳል ተመራጭ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *