ሪህ እንዳያገረሽ የሚረዱ አምስት ቁልፍ ነገሮች

የሪህ ሕመም ከአኗኗራችን ጋር ተያያዥነት ስላለው የሚከተሉት እርምጃዎች የሪህ ሕመምተኞች በሽታው እንዳይቀሰቀስባቸው ሊረዱ ይችላሉ።

1. ሪህ፣ ሰውነት ምግብን ጥቅም ላይ ከሚያውልበት መንገድ ጋር የተያያዘ ችግር በመሆኑ ሕመምተኞች የሚወስዱትን የካሎሪ መጠን በመቆጣጠር ጤናማ የሆነ ክብደት እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋቸዋል።

ከዚህም በላይ ከልክ ያለፈ ውፍረት፣ የሰውነትን ክብደት በሚሸከሙት መገጣጠሚያዎች ላይ ጫና ይጨምራል።

2. ክብደታችሁን በፍጥነት ለመቀነስ ከፍተኛ የሆነ የአመጋገብ ለውጥ ከማድረግ ተቆጠቡ፤

እንዲህ ያለው የአመጋገብ ለውጥ በደማችሁ ውስጥ ያለውን የዩሪክ አሲድ መጠን ለተወሰነ ጊዜ ከፍ ሊያደርገው ይችላል።

3. ከእንስሳት የሚገኝ ፕሮቲን አታብዙ። አንዳንዶች፣ በቀን ውስጥ የምትመገቡት ቀይ ሥጋ (የዶሮ ሥጋንና ዓሣን ጨምሮ) ከ170 ግራም መብለጥ እንደሌለበት ይናገራሉ።

4. የአልኮል መጠጥ የምትጠጡ ከሆነ ልከኛ ሁኑ። ሪህ ካለባችሁ ከነጭራሹ አልኮል አለመጠጣቱ የተሻለ ይሆናል።

5. አልኮል የሌለባቸው መጠጦችን በብዛት ጠጡ። ይህ ዩሪክ አሲድ ከሰውነት ታጥቦ እንዲወጣ ለማድረግ ያስችላል የካልሲየም ፓይሮፎስቴት ቅንጣቶች በመገጣጠሚያ ውስጥ፣

በተለይም በአጥንቶች መገጣጠሚያ ላይ በሚገኙ ሽፋኖች ዙሪያ በሚፈጠሩበት ጊዜም ተመሳሳይ ሕመም ሊኖር ይችላል።

ይሁን እንጂ እንደ ሪህ ዓይነት ምልክቶች ያሉት ይህ ሕመም ከሪህ የተለየ በሽታ ሲሆን ሕክምናውም የተለየ ሊሆን ይችላል።

አውስትራሊያን ዶክተር ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ እንደገለጸው በፕዩሪን የበለጸጉ እንጉዳዮችን እንዲሁም

እንደ ባቄላ፣ ምስር፣ አተር፣ ስፒናችና አበባ ጎመን ያሉትን የዕፅዋት ምርቶች መመገብ “ሪህ እንደሚቀሰቅስ የሚያሳይ ማስረጃ አልተገኘም።” ይህ ርዕስ የሕክምና መመሪያ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ አይደለም።

እያንዳንዱ ሕመምተኛ የሚወስደው ሕክምና የተለያየ ሊሆን ይችላል።

በተጨማሪም ሕመምተኛው ከሐኪሙ ጋር ሳይመካከር የታዘዘለትን መድኃኒት ማቆም ወይም ከፍተኛ የሆነ የአመጋገብ ለውጥ ማድረግ አይኖርበትም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *