መድሀኒቱን የተለማመደ ቲቢ (MDR TB) ምንድን ነው?

መድኃኒት የተለማመደ ቲቢ ማለት በአይን በማይታዩ ጥቃቅን ባክቴሪያዎች አማካኝነት የሚከሰት እና በመጀመሪያ ደረጃ በሚሰጠው የቲቢ መድኃኒት የማይድንና የተሻለ ህክምናና ክትትል የሚፈልግ ህመም ነው፡በአሁኑ ወቅትም በሀገራችበከፍተኛሁኔታእየተሰራጨ ይገኛል፡፡

መድሃኒት የተለማመደ ቲቢ( MDRTB) በሽታ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡

በሽታው በቀላሉ የሚሰራጭ እና በአፋጣኝ የሚዛመት ስለሆነ በተለይ በሽታ የመከላከል አቅምን እያዳከመ ለሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል፡፡

ስለሆነም በወቅቱ አስፈላጊውን ክትትል እና ሕክምና ካላገኘ ለሞት ይዳርጋል፡፡የዚህን በሽታ ስርጭት ለመቆጣጠር እና ለመግታት ስለ በሽታው በቂ ግንዛቤ እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡

እንዲሁም አንድ ሰው በህመሙ ከተያዘ በኋላ በቶሎ ወደ ጤና ተቋም እንዲሄድ እና ሕክምናውን እንዲያገኝ መረጃ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡

የሚከሰተው በዋናነት ፡-

1. የመጀመሪያ ደረጃ የቲቢ መድኃኒቶችን በአግባቡ ባለመውሰድ ወይንም ደግሞ ሙሉ በሙሉ መድኃኒቱን በማቋረጥ፡፡

2.መድሃኒቱን የተለማመደ ቲቢ ካለበት ሰው ቀጥታ ወደ ጤነኛው ሰው ሊተላለፍ ይችላል፡፡

ምልክቶቹ፡-

ሁሉም ምልክቶቹ ከመጀመሪያው የሣንባ ቲቢ በምንም አይለዩም፡፡

 ሁለት ሳምንት የቆየ ፋታ የለሽ ሳል
 ቢጫ ወይም ደም የቀላቀለ አክታ

 ደረት አካባቢ የሚሰማ ውጋት
 የምግብ ፍላጎት መቀነስ

 ክብደት መቀነስ
 ለሊት ለሊት የሚከሰት ላብ ናቸው፡፡

እነዚህ ምልክቶች በአንድ ሰው ላይ ሲታይ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ አድርጎ ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ህክምና፡-

የመጀመሪያ ደረጃውን ህክምና በአግባቡ ወስዶ ጨርሶ የሚታዩ ምልክቶች ካልጠፉና የመሻል ምልክቶች ከሌሉ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድና አስፈለጊውን ምርመራ በማድረግ ህክምናውን መጀመር ያስፈልጋል፡፡

 ሕክምናው የሚፈጀው ጊዜ 24 ወራት(ሁለት ዓመት) ነው፡፡
 ከመጀመሪያው የተሻለ ሕክምናና ክትትልና ይፈልጋል፡፡
 መድኃኒቶቹ የሚያስከትሉት የጎንዮሽ ጉዳት ወይም በመድሃኒቶቹ የተነሳ የሚመጡ ችግሮችን

ለሚከታተሉ የጤና ባለሙያዎች ማሳወቅ ያስፈልጋል ፡፡

 አስፈላጊውን ምርመራዎች በጊዜው በመገኘት መፈጸም
 ሕክምናው የሚሰጠው ያለምንም ክፍያ(በነጻ) እንደሆነ ማወቅ፡፡

መከላከያ መንገዶች፡-

የMDR TB ታማሚዎች ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

 በማሳልና በማስነጠስ ወቅት አፍን አና አፍንጫን በአግባቡ መሸፈን፡፡
 አክታውን ክዳን ባለው ዕቃ ውሰጥ አጠራቅሞ በአግባቡ ማስወገድ፡፡

 የምግብ ዕቃዎችን/ኩባያ፣ማንኪያ ፣ሹካ ለሕመምተኛው ለብቻው እንዲጠቀም መድረግ
 በመኖሪያ አካባቢ በሕዝብ ትራንስፖርት ውስጥ መስኮት በመክፈት በቂ የአየር ዝውውርና ብርሀን እዲኖር ማድረግ

 ህመምተኛው ሕክምናውን እስኪጨርስ ድረስ ከህጻናት እና አስታማሚዎች ጋር ያላቸውን ቅርበት መቀነስ
 በፍቃደኝት ላይ የተመሰረተ የኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረግና ተገቢውን የሕክምና ክትትል ማድረግ ናቸው ፡፡

የቲቢ በሽታን አስመልክቶ የተሳሳቱ አመለካከቶች

• ህክምናውን ጀምሮ ከሃኪም ትእዛዝ ውጪ ማgረጥ ፡፡
• የቲቢ በሽታ በባህል ሕክምና ይድናል ብሎ ማሰብ ፡፡
• ቲቢ የሚመጣው በብርድ ነው ብሎ ማሰብና ሌሎችም ናቸው

የባለሙያ ምክር

 የቲቢ በሽታን ቀድሞ መከላከልን ባህል ማድረግ
 ምልክቶቹ የሚታዩ ከሆነ ፈጥኖ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ

 መድሃኒቱን ሳያቋርጡ እስከ መጨረሻው በአግባቡ ወስዶ ማጠናቀቅ
 የሓኪምን ሙያዊ ምክር መቀበል መከታተልና መተግበር

 በህክናው ወቅት በቂ እረፍት ማድረግና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
 የኤች ኤ ቪ ምርመራ ማድረግ

 ከቤተሰብ መካከል ማንኛው አይነት የህመም ምልክት ከታየበት ቶሎ ብሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *