የጠ/ሚው የመቀሌ ጉዞ የፈጠረው ዉዝግብ እንደቀጠለ ነው

የጠ/ሚው የመቀሌ ጉዞ የፈጠረው ዉዝግብ እንደቀጠለ ነው

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ መቀሌ በመጓዝ ንግግር ካደረጉ በሗላ ያካበባቸው ዉዝግብ እንደቀጠለ ነው። ጠ/ሚ አብይ አህመድ ወደ ትግራይ ክልል በመጓዝ ከህወሃት ባለስልጣናት፣ከህወሃት ታጋዮችና የጦር ጉዳተኞች ብሎም ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች ጋር በመሰባሰብ ያደረጉት ንግግርር የሰላ ትችት እንዲሰነዘርባቸው ማድረጉ ታዉቋል።

ጠ/ሚው ባደረጉት የትግርኛ ንግግርና በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የቀድሞው የትግራይ ታጋዮችን ሚናን በማዳነቅ መናገራቸውና፤ የወልቃይትን የማንንነት ጥያቄ ዲያስፖራ የሚለኩሰው እሳት መሆኑን ለማመላከት መጣራቸው፤ አገራዊ ለሆኑ አንገብጋቢ ጉዳዮች ያላቸው ግንዛቤ ምን ያህል ነው? የሚል ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል።

ትግራይን ለማስገንጠል ወደ ደደቢት ጫካ የገቡት ታጋዮች አያሌ መስዋእትነትን በመክፈላቸው ዜጎች የሚያሳዩት አዘኔታ ቢኖርም፤ ታጋዮቹ ከሻእብያ ጋር በመተባበር ኤርትራን በማስገንጠልና ኢትዮጵያን ወደብ አልባ በማድረጋቸው ታሪካዊ ተወቃሽ መሆናቸው ተዘንግቷል የሚሉ ወገኖች ተቃዉሞ ተሰምቷል።

ወደደቢት ጫካ በመግባት እራሳቸውን «ወያነ ሐርነት ትግራይ» ብለው የሰየሙት ታጋዮች ለ27 አመታት የዘለቀ አምባገነነዊ ስርዓትና በመዘርጋት፣ወጣቱን በባድመ ጦርነት በመማገድ፣ህዝብን በማሰር፣በመግደል፣በማሰቃየት፣ያገርን ሐብት በመዝረፍ የተሰማሩ በመሆናቸው እንደምን ጠ/ሚው አድናቆታቸውን ያዥጎደጉዳሉ? የሚሉ የቅዋሜ ድምጾች ተሰምተዋል።

ጠ/ሚው በየከተማው እየዞሩ የምርጫ ቅስቀሳ መሳይ ንግግር ከማድረጋቸው በፊት ተረጋግተው የካቢኔ ለዉጥ ሊያረጉ ይገባ ነበር በማለት ሐሳባቸውን የሚሰጡ ሰዎች በበኩላቸው መስዋእትነት የተከፈለበትን የወልቃይት ጥያቄ አመናምኖ የልማትና የእድገት ጉዳይ እንደሆነ ለማመላከት መሞከሩ በወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ላይ የተሰነዘረ ስላቅ ነው ሲሉ ይተቻሉ።

የመከላከያ ሰራዊቱን፣ደህንነቱን፣ያገሪቱን መዋእለ-ንዋይና የመገናኛ ብዙሗንን ህወሃት በተቆጣተረበት መልኩ የጠ/ሚው ከክልል ወደ ክልል በመጓዝ የሚያደርጓቸው ንግግሮች እርስ በርስ መጣረስ ጀምረዋል በማለት የሚያስረዱ አካላት «የታየው የጠቅላይ ሚኒስቴር ለዉጥ በጭብጨባና በጩኸት የታጀበ ቃልኪዳን የሚዘረገፍበት፤ ለዉጥ በተግባር የማይታይበት ፖለቲካዊ ትርዒት እንዳይሆን» ሲሉ ስጋታቸድውን አክለው ይገልጻሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *