Day: April 16, 2018

ወልቃይት የማነው? (ኤርሚያስ ቶኩማ)

የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር በትግርኛ አጠራሩ ህወሀት ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ግፎችን በወልቃይት ህዝብ ላይ እንደፈፀመ ማስረጃዎች ያስረዳሉ። በ1984 በአካባቢው ይኖር የነበረው የወልቃይት ተወላጅ ቁጥሩ ከ83,000 በላይ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ይህ አሐዝ ወደ 48,000 እንደወረደ ለማወቅ ተችሏል 35,000 ያህል የወልቃይት ጠገዴ ፀለምትን ህዝብ ምን ዋጠው መቼም ሁሉም ሠው በእርጅና […]

ባለፉት አመታቶች የወጣቱ ደም ደመከልብ የሆነው አዲስ የእጅ አዙር አምባገነኖችን ለመፍጠር አይደለም።

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ የትግሉ አነሳስና የትግሉ ግብ ወያኔን ማስወገድ ነው ። የፈዘዘ ቀረ እንደደነዘዘ። ባለፉት አመታቶች የወጣቱ ደም ደመከልብ የሆነው አዲስ የእጅ አዙር አምባገነኖችን ለመፍጠር አይደለም። ወያኔ ከየአቅጣጫው የምያየውን የተስፋ ድጋፍ ለፖለቲካ ፍጆታ እንደሚጠቀምበት ልናውቅ ይገባል። የአብይ ጉዳይ በፍጹም ሊያነጋግረን አይገባም። ዋናው ጉዳያችን የሆነውን ወያኔን ከስሩ ነቅሎ የመጣል ትግላችንን አጠናክረን […]

በሆሳእና ከተማ ዋቻሞ ዩነቨርሲቲ በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 ያላነሱ የዐማራ ተማሪዎች ከግቢ ተባረዋል፤

በዋቻሞ ዩነቨርሲቲ በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 ያላነሱ የዐማራ ተማሪዎች ከግቢ ተባረዋል፤ የትንሳኤ በዓል ጠዋት የሚጾሙ ተማሪዎች ከቤተ ክርስቲያን ሲመጡ ምግብ ባለመዘጋጀቱ የዩንቨርሲቲውን አመራር አካላት ይጠይቃሉ፡፡ በትንሳኤ በዓል ምክንያት በክርስትና እምነት ተከታዮች የቀረበው ጥያቄ ወዲያውኑ መልኩን ቀይሮ ወደ ብሔር ግጭት ተቀይሯል፡፡ ሺፈራው ሽጉጤ በሚዘውረው ክልል በሆሳእና ከተማ በሚገኘው የዋቻሞ ዩንቨርሰቲ የትንሳኤ ዕለት […]

ከአቶ በቀለ ገርባ አጭር መልእክት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ

ከአቶ በቀለ ገርባ አጭር መልእክት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ እንዳሉት ሰላም ከፍ ባለ ድምጽ ተራራ ላይ ወጥቶ በመጥራት አይመጣም። ሰላም እንዳይኖር ያደረገው የኢህአዴግ አገዛዝ ነው። ህዝቡማ ምንጊዜም ሰላም ወዳድና ሁሌም ሰላማዊ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ለሰላሙ ዘብ ይቁም ብሎ ጥሪ ማድረግ እምብዛም ቦታ የለውም። በመሆኑም እውነተኛ ሰላም እንዲሰፍን […]

ያላስከበርከውን ማንነትን ወድቆ አታገኘውም! (ፍፁም አየነው)

ኢትዮጵያ ሀገራችን የትግል ህንጻ ናት፡፡ በተለያዩ ጊዜና ወቅት በመራራ መስዋዕትነት ስትገነባ የኖረች ፤ ዛሬም ሁልጊዜም ስትታነፅ የምትኖር የማታረጅ የማትገፋ እናት ናት፡፡ ለዚህች እናት ሀገር ያልተፈለ ዋጋ የማይከፈል መሰዋዕነት የለም፡፡ ይኽም በአፍ ተነግሮ ሳይሆን፤በተግባር በጥላቻም ሳይሆን በፍቅር የተተገበረ ነው፡፡ አማራም ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት መሃንዲስነቱን በእነዚያ ዘመናት በተግባር አረጋግጧል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ […]

ጋና መስጊዶችና አቢያተክርስቲያናት ከድምጽ ማጉያ ይልቅ ዋትሳፕ እንዲጠቀሙ የሚያዝ ህግ ልታወጣ ነውI

የጋና ባለስልጣናት መሲጊዶችና አቢያተክርስቲያናት ለጸሎት መጥሪያ የሚጠቀሙትን የድምጽ ማጉያ በመተው በዋትሳፕ እንዲገለገሉ የሚያዝ ህግ ለማጽደቅ ከጫፍ ደርሰዋል። በተለይም በጋና ዋና ከተማ አክራ የሚገኙ የእምነት ቤቶች በጸሎት ሰአት የሚያወጡት ከፍተኛ የድምጽ መጠን በማህበረሰቡ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ነው የሀገሪቱ አካባቢ ባለስልጣን የተናገሩት። “አሁን ይህን የማስቆሚያው ሰአት ነው።” በማለት የእምነት […]

ሴካፋ በኢትዮጵያ ላይ የ5 ሺህ ዶላር የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ

ሴካፋ በኢትዮጵያ ላይ የ5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ። ቅጣቱ የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድን ትናንት በሴካፋ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ከሶማሊያ አቻው ጋር ባደረገው የማጣሪያ ጨዋታ ያልተገቡ ተጫዋቾችን ተጠቅሟል በሚል የተላለፈ ነው ተብሏል። ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪም የትናንቱ ጨዋታ ውጤት ተሰርዞ ሶማሊያ በፎርፌ እንድታሸንፍም ወስኗል። በትናንት ጨዋታ ቡድኑ ሶማሊያን 3 […]

ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የስኳር ሕመም ምልክቶች

የስኳር ሕመምን በተመለከተ በተለያዩ የጤና ምክር መስጫ ፕሮግራሞች ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ የማስጨበቻ ሥራዎች እየተሰሩ ናቸው፡፡ ከዚህ በታች ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የሕመሙን ጠቋሚ ምልክቶች እንግራችኋለሁ፡፡ ስለስኳር ሕመም በዝርዝር በቅርቡ የሚያስገባችሁ ይሆናል፡፡ 1) ከተለመደው ጊዜ በተለይ ውሃ መጠማትና በተደጋጋሚ የውኃ ሽንት መምጣት፡፡ የስኳር ሕመም ለኩላሊት ችግር በማጋለጥ ቀዳሚ ደረጃን የሚይዝ ሲሁን […]

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለ150 የጎዳና ተዳዳሪዎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ሰጠ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ከአራዳ ኬር ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በመዲናዋ ለሚገኙ 150 የጎዳና ተዳዳሪዎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት መስጠቱን አስታወቀ፡፡ ሆስፒታሉ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው ተብሏል። ሆስፒታሉ ተከታታይ ህክምና ማግኘት የሚያስችላቸውን ስርዓት በመዘርጋት ካሉባቸው የጤና ችግሮች እንዲፈወሱ ሙሉ የህክምና አገልግሎት እየሰጣቸው መሆኑንም ዶክተር […]

ውጤታማ ባልሆነ የተንዛዛ ስብሰባ የሚባክነውን ጊዜና ንብረት መቀነስ – ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ

በስነምግባር የታነጸ ሙያውን አክብሮ ለሃላፊነት ክብር ሰጥቶ የሚያገለግል የመንግስት ሰራተኛና አመራር እንዲፈጠር የመንግስት ጽኑ ፍላጎት መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ”የፍቅርና የአንድነት ኪዳን” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ በሚሌኒየም አዳራሽ በሃገሪቱ ለተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በስነምግባር የታነጸ የአገልግሎት መንፈስ የተላበሰ ሰራተኛ እንዲኖር ጉቦና የጥቅም ሽርክና ዝምድናና አድሏዊ […]