የወልዲያን ክለብ ለማፍረስ የተቃጣው ሴራ!

ወያኔዎች የወልዲያን ክለብ በቂም በቀል ለማፍረስ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሱ ቢመስልም ክለባችን እንዳይፈረስ የሞት የሺረት ትግል ማካሔድ አለብን፡፡

ወያኔዎች ወልዲያን ለማፍረስ የተጠቀሙት አሰልጣን ዘማርያም ወልደጊወርጊስ የተባለን ወያኔ ነው፡፡

ይህ ሰው የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ በነበረ ጊዜ በመታመሙ ምክንያት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች 600 ሺህ ብር አዋጥተው ውጭ አገር ሒዶ እንዲታከም አድርገውታል፡፡

ሆኖም ይህ ጡት ነካሽ የሆነ ወያኔ የወልዲያን ክለብ ለማፍረስ የመጨረሻ ካርዱን ስቧል፡፡ ወልዲያን ለማፍረስ የተደረጉ ሴራዎች፤

ሀ/ በፋሲልና በወልዲያ መካከል በነበረው ጨዋታ የታየው የዐማራ አንድነት ቀን ሳይደፍን እንዲደፈርስ አስቀድሞ የታቀደ ነበር፡፡

በመሆኑም በሕወሓት ተመልምለው አንድ አካባቢ የተቀመጡ ወያኔዎችና ቅጥረኞች ጨዋታውን ለማፍረስ ሰዐት ቢጠብቁም እድል አላገኙም ነበር፤ ሆኖም ጨዋታው ሊያልቅ 3 ደቂቃዎች ያክል ሲቀሩ ዳኛው የሰጣት የቅጣት ምትን ምክንያት በማድረግ አሰልጣኙ ዘማሪያም ሜዳው ውስጥ ዘሎ ሲገባ እነዚህ ምልምሎች ተከተሉት፡፡

ዋናው ዓላማ ዐማራውን እርስ በእርስ ለማጫረስ ቢሆንም የዐማራው ወጣት ሴራውን አከሸፈ፤ በዚህ መካከል ይኼው ተልአኮውን ይዞ የገባው ዘማሪያም እና ዳኞች ጉዳት ደረሰባቸው፡፡ ሕዝብ ግን አንድነቱን አስጠብቆ ወጣ፡፡ ,

ለ/ መቀሌ ያለው ድምጸ ወያኔን ጨምሮ ቅጥረኞ ሚደያዎች የወልዲያ ከነማ ላይ ተከታታይ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ተካሔዱ፡፡

በዚህም የክለቡን ስም የሚችሉትን ያክል ክለቡ ላይ እገዳ እንዲጣልበት ዘመቻው ተጧጧፈ፡፡

አዲግራትና መቀሌ በድንጋይ ደጋፊ ከደጋፊ በድንጋይ ሲጋመሱ ምንም ያላለው ሚዲያ ጉዳዩን ወልዲያ ለጠብ ብቻ የተፈጠረ እስኪመስል ድረስ ክለቡን አልፎም ዐማራውን (የወልዲያን) ሰሙን አጠፉት፡፡

ሐ/ ዛሬ ደግሞ እነዘማርያም የተባሉት ባለተልእኮ ጡት ነካሾች የሌሉ ተጫዋጮችን ሁሉ ስም በመጻፍና አስመስለው በመፈረም ወደ ክለቡ ቢሔዱ ሕይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚወድቅ የሚያትት ደብዳቤ በመጻፍ ለፌደሬሽኑ አስገቡ፤ እንደ ብስራት ያሉት ቅጥረኛ ጣቢያዎችም ዜናውን ሲያስተጋቡት ዋሉ፡፡

ቢያንስ እንኳ ሁሉም ተጫዋቾች ፈርመው ማስገባታቸውን ሳያጣራ በመገናኛ ብዙሃን ለቀቁት፡፡

ይህ ሁሉ የሚሆነው ትግሬዎች እንደፈለጉ በሚያደርጉት ፌደሬሽን ክለቡን ለማሳገድ ወይም ለማፍረስ ሕጋዊ ከለላ ለመስጠት ነው፡፡

ሕወሓት እንዲሕ ያሉ ሕዝባዊ አጀንዳዎችን በተለያዩ ጊዜያት በመፍጠር ኅብረተሰባዊ እረፍት መንሳት የሚለውን ፕሮጀክቷን ማስቀጠሏ ነው፡፡

ከእንዲህ ያሉ እኩይና ቂመኞች ጋር እንዴት አብሮስ መኖር ይቻላል?

ጠላቶቻችን እንጋፈጣለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *