የለውዝ ቅቤ አለርጂን መከካል የሚያስችል ክትባት ይፋ ተደረገ

የለውዝ ቅቤ አለርጂን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት መገኘቱን ተመራማሪዎች አስታወቁ።

ክትባቱ ከምግብ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አለርጂዎችን መቆጣጠር ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ይህም በአይጥ ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ሙከራ እንደተረጋገጠ ነው የተነገረው።

በዚህም ክትባቱ የቆዳ ቁስል እና የአተነፋፈስ ችግር በነበረባቸው አይጦች ላይ በተደረገ ሙከራ ከሁለት ሳምንት በኋላ ውጤት እንዳሳየ ተነግሯል።

ይህ ክትባት የአለርጂ በሽታን ለመቋቋም የሚያስችል አዲስ ዜዴ መሆኑንም ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

ክትባቱ አለርጂ ከተከሰተ በኋላም መቋቋም እንዲቻል ከማድረግም በተጨማሪ ለአለርጂ ምክንያትና መነሻ የሚሆኑትን ህዋሳት ለመቆጣጠር እንዲያስችል ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *