አሳሪዎቼ ከእኔ የሚፈልጉትን አውቀዋለሁ ጊዜው ሲደርስ ለህዝብ እናገራለሁ። ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ

አሳሪዎቼ ከእኔ የሚፈልጉትን አውቀዋለሁ ጊዜው ሲደርስ ለህዝብ እናገራለሁ።

ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ከቂሊንጦ እስር ቤት

እኔ የመጣሁት ሃገሬን እና ህዝቤን ለማገልገል ነው ሃብት ለማካበት አይደለም ለሃብት ቢሆን ኖሮ ፈረንጆች ብዙ ዶላር እየከፈሉ እየለመኑ ነበር የሚአሰሩኝ።

ብፈታም በሃገሬ ተበድያለሁ ብዬ ፈርጥጨ አልሄድም በሃገር እና በህዝብ ቂም አይያዝም ይቅር መባባል ያስፈልጋል።

አሳሪዎቼ እኔ ላይ ይሄንን ሁሉ በደል ለምን እንደሚአደርሱብኝ አውቀዋለሁ ከእኔ የሚፈልጉት ያልሰጠኋቸው ነገር አለ ወደፊትም አልሰጣቸውም።

ጊዜው ሲደርስ ለህዝብ እናገራለሁ።

በርቱ በተለይ ወጣቶች የብሄር ፖለቲካን መታገል አለባችሁ ከአሁን በኋላ በሃገራችን እረስ በርስ ግጭት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማብቃት አለበት አንድ ከመሆን የተሻለ አማራጭ የለንም።

መልካም የፋሲካ በአል ይሁንላችሁ።

ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ በእለተ ፋሲካ ያስተላለፉት መልክት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *