ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ረፋድ ላይ በፋሲለደስ ስታዲየም ባሰሙት ንግግር ጎንደር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያላትን ቦታና እና የስኬት እና የጀግንነት ታሪኮች ካነሳሱ በኃላ አሁንም ህዝቡ “በትዕግስትና በአርቆ አሳቢነት” ከጎናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል። “የስልጣኔ መሰረት፣ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ጌጥና የኩሩ ህዝብ ምድር” የሚሉ ሙገሳዎችን ያሰሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የነዋሪዎችን ፍላጎት ለማሳካት የክልሉና የፌደራል መንግስት እንደሚተጉ […]