Month: March 2018

የአሁኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከባለፈው የባሰ መሆኑን የህወሓት ሊቀ-መንበር ተናገሩ

የአሁኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከባለፈው የባሰ መሆኑን የህወሓት ሊቀ-መንበር ተናገሩ ለሁለተኛ ጊዜ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከባለፈው ጋር ሲነጻጸር፣ ባስ ያለ መሆኑን ዶ/ር ደብረጽዮን ገ.ሚካኤል ተናገሩ፡፡ በቅርቡ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት እና የህወሓት ሊቀ-መንበር ሆነው የተሾሙት ደብረጽዮን፤ ይህን ያሉት ትላንት አርብ የካቲት 30 ቀን 2010 በሰጡት መግለጫ ሲሆን፤ በመግለጫቸውም ስለ […]

ቪታሚን ዲ በካንሰር የመያዝ እድላችንን እንደሚቀንስ ተገለጸ

በደማችን ውስጥ የሚገኝ የቪታሚን ዲ ክምችት በካንሰር የመያዝ እድላችንን ሊቀንሰው እንደሚችል የጃፓን አጥኚዎች አስታወቁ። ጥናቱ ያተኮረው በዋናነት በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ መሆኑ ተነግሯል። በጥናቱ ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት እስከ 69 ዓመት በሚገኙ 33 ሺህ 736 ሰዎች ላይ መካሄዱን ገልጸዋል። ታሳታፊዎችም የጤና ታሪካቸውን መረጃ ለአጥኚዎቹ የሰጡ ሲሆን፥ በተጨማሪም የቪታሚን ዲ ክምችት ለማወቅ የደም […]

የደም ግፊት፣ በደም ውስጥ ያለን ስብ ለመቀነስ፣ ኢንፌክሽንና ጉንፋንን ልንከላከል የምንችልባቸው መንገዶች

ነጭ ሽንኩርት፣ ሎሚ እና ዝንጅብል በዉሃ ውስጥ አንድ ላይ ደባልቆ መጠቀም የደም ግፊት፣ በደም ውስጥ ያለ ስብን ለመቀነስ እንዲሁም ኢንፌክሽንና ጉንፋንን ለመከላከል እንደሚረዳ ከወደ ጀርመን ሀገር የወጣ መረጃ ያመለክታል። በተጨማሪም የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምም ከፍ እንዲል እንደሚረዳም ተጠቁሟል። ውህዱን ለማዘጋጀት የሚስፈልጉን ነገሮች አራት ራስ ነጭ ሽንኩርት፣ አራት ያልተላጠ ሎሚ፣ አነስ […]

አወሊያ ያፈራቻቸው ታላቋን ልጇን በዛሬው ዕለት በድንገት በሞት አጣች!

አወሊያ ያፈራቻቸው ታላቋን ልጇን በዛሬው ዕለት በድንገት በሞት አጣች! ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጁኡን! ለረጅም አመታት አወሊያን ተቅዋምን በተለያዩ የስራ ሃላፊነት ሲያፈለግሉ የቆየው እና በመጨረሻም የአወሊያ ተቅዋም ም/ስራ አስካሄጅ የነበረው ተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ መርዙቅ በዛሬው ዕለት በድንገት ወደ አኬራ ሄዱ! ብቸኛው የሙስሊሞችን ተቅዋም አወሊያን በተለያዩ የስራ ዘርፎች የአወሊያን ማህበረሰብ እና […]

ኮማንድ ፖስቱ በርካታ ሰዎችን እያሰረ እንደሚገኝ ታወቀ

ኮማንድ ፖስቱ በርካታ ሰዎችን እያሰረ እንደሚገኝ ታወቀ በኢትዮጵያ ለእስር የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች አመለከቱ፡፡ በተለይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በፓርላማ ከጸደቀ በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መታሰራቸውን የገለጹት መረጃዎች፤ የእስረኛው ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየናረ መምጣቱንም መረጃዎቹ ይገልጻሉ፡፡ በዚህ ሳምንት ብቻ ከኦሮሚያ ክልል በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን […]

በአማራ ክልል ትጥቅ የማስፈታት ሙከራ እየተደረገ መሆኑ ታወቀ

በአማራ ክልል ትጥቅ የማስፈታት ሙከራ እየተደረገ መሆኑ ታወቀ በአማራ ክልል ሰዎችን ትጥቅ ለማስፈታት እንቅስቃሴ መጀመሩ ታወቀ፡፡ ‹‹ የጦር መሳሪያ አያያዝን ማስተካከል›› በሚል ሸንጋይ ቃል የተጀመረው እንቅስቃሴ አርሶ አደሩን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል መሳሪያ ለመንጠቅ ያለመ እንደሆነ የገለጹት መረጃዎች፤ ይህንንም ለማሳከት ስልጠና መሰጠት መጀመሩን ከመረጃዎቹ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ስልጠናው ከሚሰጥባቸው የክልሉ […]

የዋልድባ መነኮሳት በእስር ቤት እየተፈጸመባቸው ያለውን ግፍ ዘረዘሩ

የዋልድባ መነኮሳት በእስር ቤት እየተፈጸመባቸው ያለውን ግፍ ዘረዘሩ የዋልድባ መነኮሳት በእስር ቤት እየተፈጸመባቸው ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተያዘ፡፡ መነኮሳቱ ታስረው በሚገኙበት ቃሊቲ እስር ቤት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ ለፍርድ ቤት ሲያመለክቱ የቆዩ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም ችሎት ቀርበው፣ እየደረሰባቸው ያለውን በደል ዘርዝረዋል፡፡ መነኮሳቱ ከዚህ […]

ኮማንድ ፖስቱ የክልል የሥልጣን መዋቅሮችን መቆጣጠሩ ተጠቆመ

ኮማንድ ፖስቱ የክልል የሥልጣን መዋቅሮችን መቆጣጠሩ ተጠቆመ ራሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈጻሚ እያለ የሚጠራው ኮማንድ ፖስት የክልሎችን የስልጣን መዋቅሮች ከጥቅም ውጭ አድርጎ እንደተቆጣጠረ ታወቀ፡፡ በተለይ አዋጁ ከጸደቀ በኋላ፣ በክልሎች የተዘረጋው የስልጣን መዋቅር በኮማንድ ፖስቱ ቁጥጥር ስር በመሆኑ፤ የክልል አስተዳዳሪዎች በኮማድ ፖስቱ ትዕዛዝ ስር እንደሚገኙ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ፣ ኮማንድ […]

አሜሪካኖች የተለሳለሰ ሽግግር ይፈልጋሉ፤ ወሳኙ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኃይሎች ናቸው” ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሰ

በኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ ድንጋጌን ተከትሎ የአሜሪካ ኤምባሲ ባልተለመደ መልኩ ጠንከር ያለ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። ከዚያ በመቀጠል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሬክስ ቲለርሰን በኢትዮጵያ ለዓመታት ስለዘለቅው ተቃውሞና በሃገሪቱ ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ ከባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ሃገር ውስጥ ገብተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ጉብኝት በተመለከተ ያነጋገርናቸው ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሰ እንደሚሉት […]

የኬንያው ፕሬዝዳንት ከተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ ጋር እርቅ ለማድረግ ተስማሙ

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ እርቅ ለማድረግ ተስማሙ። ያለፈውን ምርጫ ተከትሎ ሁለቱ ተቀናቃኞች ከባድ ፍጥጫ ውስጥ ገብተው የነበረ ሲሆን ከምርጫው በኋላ በተፈጠረው አለመረጋጋት 150 ሰዎች ሞተዋል። ካለፈው ምርጫ ውዝግብ በኋላ ባላንጣዎቹ በይፋ ውይይት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው። ኡሁሩና ራይላ ከተወያዩ በኋላ በቀጣይ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ቃል ገብተዋል። ከጥቂት […]