የአድማ በታኝና የፖሊስ ስምሪት ጨምሯል

መረጃ፦

የአድማ በታኝና የፖሊስ ስምሪት ጨምሯል

ትላንት የተጀመረውን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ በዛሬውእለት አዲ አባባን በሚያዋስኑ ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ የፖሊስና የ አድማ በታኝ ስምሪት መኖሩ ታወቀ።

በፉሪ፣በወልቴ፣ኖክና ጀሞ አካባቢ ዛሬ በማለዳው የሰፈሩትን ፖሊሶች ፎቶ ግራፍ አንስተው የላኩልን ያካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹልን የስራ ማቆም አድማው ዛሬም ሙሉ ለሙሉ እየተከናወነ ይገኛል።

ያካባቢው ነጋዴዎች የንግድ ድርጅታቸውን ካልከፈቱ ከቄሮ ጋር የሚፈጥር ችግር እንደሌለ ያስረዱን ምንጮቻችን ፖሊስና አድማ በታኝ በጠዋቱ መጥቶ መስፈሩ ሆን ተብሎ ሁከተን ለመቀስቀስ የታቀደ በመሆኑ ቄሮና ነዋሪዎች ይህንን ጸብ አጫሪነት ልብ ሊሉት ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ፖሊሶቹና አድማ በታኞቹ ህስብን ለማሸማቀቅ ቢሰፍሩም ህዝቡ ከፍርሃት ተላቆ ህወሃት የወሰደበትን ነጻነት ለማስመለስ በዘርና በሀይማኖት ሳይለያይ እየተባበረ ነው ሲሉ እነዚሁ የቢቢኤን ምንጮች አሳውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *