ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ ምክሮች

ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ ምክሮች

የቦርጭን ችግር ቦርጫሞች ይረዱታል፡፡

ቦርጫም መሆን ማለት ትልቅ ቋጥኝ ተሸክሞ መዋል ማደር ነው፡፡

እንቅስቃሴን ከመገደብ አልፎ አያሌ የጤና ችግሮችን ያስከትላል… ለምሳሌ እንደ ልብ ሕመም፣ የስኳር ሕመም፣ የደም ግፊት መጨመር እና ከፍተኛ የኮሌስትሮል ክምችትን ይፈጥራል፡፡

እባክዎ… ቦርጫም ባይሆኑ ሼር ያድርጉት፤ ለቦርጫም ወዳጆችዎ ይደርሳቸዋል፡፡

►መንስኤው

በአብዛኛው ስብ የሚከማችበት ቦታ ሆድ አካባቢ ሲሆን ይህም በአማርኛው ቦርጭ ብለን የምንጠራው ነው፡፡ ቦርጭን ሊያመጡ የሚችሉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

✔ ሊተኙ ሲሉ መመገብ
✔ ሰዓትን ጠብቆ አለመመገብ
✔ በሰውነታችን የሚገኙ ሆርሞኖች ለውጥ
✔ ጭንቀት
✔ ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
✔ በተፈጥሮ የሚመጣ

► ቦርጭን ለማጥፋት መፍትሄው

✔ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ ብርጭቆ ሎሚ ያለው ውኃን ጠዋት መጠጣት
✔ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት፡- በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገር ምክንያት አላስፈላጊ ስብን የማስወገድ አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

✔ ስብ የማቃጠል ችሎታ ያላቸው ምግቦችን መመገብ፡- እነዚህም እንደ ብሮክሊ፤ካሮት፤ጎመን ያሉ አትክልቶቸ፤ እንዲሁም እንደ ፖም፤ ሃብሃብ፤ ፓፓዬ ያሉ ፍራፍሬዎችን ማዘውተር
✔ ጤናማ የሆነ አመጋገብ እንዲኖረን ማድረግ ፡- የተመጣጠነ እና አትክልት የበዛበት የምግብ ባሕልን ማዳበር
✔ በቀን ውስጥ የምንጠጣውን የውኃ መጠን መጨመር
✔ ቁርስን በሚገባ መመገብ፡- ይህን ማድረግ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማንና ማስታገሻ የሚሆኑ ተጨማሪ ስኳር እና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች እንዳንመገብ ያደርጋል፡፡

✔ የአካል ብቀት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ዋና መዋኘትን ማዘውተር በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል የእግር መንገድ መሄድ
✔ እንቅልፍ አለማብዛት
✔ ጭንቀት ማስወገድ
✔ ለስላሳ መጠጦችን አለማዘውተር ናቸው፡፡


ምንጭ – ዶ/ር ሆነሊያት እና ዶ/ር አለ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *