ስበር ዜና

አቶ በቀለ ገርባ ከእስር ተለቀቁ
አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ስድስት ታሳሪዎች ዛሬ ከእስር መለቀቃቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

ፓርቲያቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስም መለቀቃቸውን መስማታቸውን ገልፀዋል።

ፋና ጨምሮ እንደዘገበውም አቶ ጉርሜሳ አያና፣ አዲሱ ቡላላ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ ጌቱ ጋሩማ፣ ተስፋዬ ሊበን እና በየነ ሩዳ በዛሬው እለት ከእስር ተለቀዋል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት (ኦፌኮ) ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ በሽብር ተከሰው በእስር እንደቆዩ የሚታወስ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *