Day: February 13, 2018

የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች እና የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ሶስት ቀናትን የፈጀ ድርድር በኬንያ ናይሮቢ አድርገዋል፡፡ በኬንያ ባለስልጣናት አደራዳሪነት በሚስጢራዊ ቦታ የተከወነው የሁለቱ ወገኖች ንግግር ከ30 ዓመታት በላይ ለቆየው ጠብ፣ለብዙዎች ሞትና መፈናቀል ሰበብ ለሆነው ፍጥጫ እልባት ከመስጠት አልፎ በመላው የአፍረቃ ቀንድ የሰላምና ደህነት ሁኔታ የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለው የገመቱ ተንታኞችን ትኩረት ስቧል-ሙሪዚ ሙቱጋ አንዱ ናቸው፡፡ ሙሩዚ ሙቱጋ ደም አፋሳሽ ግጭቶች እንዳይከሰቱ በከላለከል፣ቁጥራቸውን በመቀነስ እና ተፈጥረው ሲገኙም መፍትሄ በመፈለግ ስራ የተሰማራው የኢንተርናሽናል ክራይስ ግሩፕ የአፍሪቃ ቀንድ ከፍተኛ ተንታኝ ናቸው፡፡የሁለቱ ወገኖች የአሁን ንግግር ዓመታትን ከፈጀው ግጭት አንጻር ያለውን አንድምታ አጋርተውኛል፡፡ ‹‹ይሄ ረጅም ጊዜን ያስቆጠረ፣የተወሳሰበና ጥልቅ ስር መሰረት ያለው ግጭት መሆኑን እናውቃለን፡፡ባለፉት ጊዜያት ሰለማዊ መፍትሄ ለማግኘት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ሁለቱም ወገኖች ጉዳዩ በጦር ሊፈታ እንደማይችል ወደ መገንዘቡ እንደመጡ አስባለሁ፡፡ስለሆነም የአሁኑን ጥረት በመልካምነት ሊቀበሉት የሚገባ ነው፡፡›› የኢትዮጵያ መንግስት እና የአቦነግ ግጭት ለብዙ ንጹሃን ሞት፣አካል መጉደል እና ማፈናቀል ምክንያት ስለመሆኑ በተለያዩ ጊዜያት በመብት ተሟጋች ድርጅቶች ዘንድ ተተንትኗል፡፡የሁለቱ ወገኖች ድርድር በተሰማበት ወቅት -ድርድሩ ከፖለቲካዊ አጀንዳው ጎን ለጎን የሰብአዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸውን ወገኖች ዕጣ እና ፍትህ ጉዳይም ሊያካትት ይገባል የሚሉ አስተያየቶች በተለያዩ ገጾች ላይ ተነበዋል፡፡ Somalia Äthiopien Viehzucht-Nomaden (DW/J. Jeffrey) ሙሩቲ ሙቱጋ እንዲህ ያለውን ነጥብ መነሳቱን በአወንታዊነት ይቀበሉታል ፡፡ሆኖም ጥያቄው ሰላም ይቅደም ወይስ ፍትህ? ከሚለው የተሻለውን ቅደም ተከተል ከመምረጥ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ይጠቅሳሉ፡፡ ‹‹ የቅደም ተከተል ጥያቄ ይመስለኛል፡፡መጀመሪያ ሰላም እንዲረጋገጥ አድርገህ ቆየት ብለህ ሁኔታዎች ሲፈቅዱ እንደሁለተኛ ርምጃ በተፈጸሙ የከፉ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ዙሪያ ችሎት እንዲቋቋም ትጥራለህ ወይስ ሌላ፡፡ሰላም እና ፍትህ ተነጣጥለው የሚቆሙ ጉዳዮች አይደሉም ሁኔታው የትኛው ይቅደም የሚል የቅደም ተከተል ጥያቄ ነው፡፡›› የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦብነግ የድርድር ዜና የተለያዩ ስጋቶች ተደቅነውበታል፡፡የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት በአደጋ ውስጥ ይጥላል የሚሉ ድምጾች ከኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ዘንድ ተሰምተዋል፡፡ሊታረቅ የማይችል የሚመስለው የሁለቱ ቡድኖች ፍላጎት በምን ሁኔታ ወደ አንድ መዳረሻ ሊመጣ እንደሚችል በርካታ ጥያቄዎች አሁንም አልተመለሱም-የድርድሩ ውጤታማነትም ገና አለየለትም፡፡ የኢንተርናሽናል ክራይስ ግሩፕ ከፍተኛ አጥኚ ሙሩዚ ሙቲጋ ሁሉም አካላት የጋራ መግባቢያ ነጥብ ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት ልክ የጉዳዩ ውጤታማነት አንደሚወሰን ዕምነታቸውን ያገራሉ፡፡ ‹‹በስተመጨረሻ ሚዛን የሚደፋው ጉዳይ የሁለቱ ወገኖች ቅንነት ነው፡፡ሁለቱም ጎኖች የየራሳቸው የሆነ ፍላጎት አላቸው፡፡ሆኖም በትንሹ በሰላም ጥያቄ፤በተወሰነ ደረጃ የማህበረሰብ ስምምነት ጥያቄ ሁለቱን ወገኖች ለድል የሚያበቃ የጋራ ነጥብ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ሆኖም በተቃዋሚ ወገኖች ዘንድ የሚነሱ ማሳሰቢያዎችም በቁምነገር መጤን አለባቸው -በቸልታ ሊታለፉ አይገባም፡፡››

በቡድን ስር ለመዋጋት ከጎርጎሮሳዊው 2012 አንስቶ ከአውሮጳ ወደ ሶሪያ እና ኢራቅ የሄዱት ቁጥር 5 ሺህ ይደርሳል። እስካሁን 1500 እንደሚሆኑ የሚገመቱ «የውጭ አሸባሪ ተዋጊዎች» የሚባሉት እነዚሁ የተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት ዜጎች ወደ አውሮጳ ተመልሰዋል። ከተመላሾቹ አንድ ሦስተኛው ከቤልጂግ ከጀርመን እና ከኔዘርላንድስ የሄዱ መሆናቸውን ባለፈው ሳምንት ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ ይፋ የሆነ አንድ ጥናት […]

ድርድሩ ሶስት ቀናትን ወስዷል

የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች እና የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ሶስት ቀናትን የፈጀ ድርድር በኬንያ ናይሮቢ አድርገዋል፡፡ በኬንያ ባለስልጣናት አደራዳሪነት በሚስጢራዊ ቦታ የተከወነው የሁለቱ ወገኖች ንግግር ከ30 ዓመታት በላይ ለቆየው ጠብ፣ለብዙዎች ሞትና መፈናቀል ሰበብ ለሆነው ፍጥጫ እልባት ከመስጠት አልፎ በመላው የአፍረቃ ቀንድ የሰላምና ደህነት ሁኔታ የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለው የገመቱ […]

መንግስት ከኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር ጋር ያደረገው ምስጢራዊ ድርድር ሀገሪቱን ወደ ባሰ ቀውስ የሚመራ ነው -ምሁራን

ዋዜማ ራዲዮ- መcollageንግስት ከህዝብ ተሸሽጎ ከኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ጋር የሚያደርገው ድርድር አላማው የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት መደራደሪያ አድርጎ ማቅረብ ብሎም የህወሀት ሀገር የመገንጠል ዝንባሌ ምልክቶች ናቸው ሲሉ የፖለቲካ ምሁራን አሳሰቡ። ዶ/ር ዲማ ነገዎ፣ ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው እና ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በጋራ በፃፉት አስተያየት በናይሮቢ በመንግስትና በኦብነግ መካከል የተደረገው ድርድር ቅንነት […]

የራስ ምታት ስሜቶችና መከላከያ መንገዶች

ራስ ምታት በአብዛኛው የተለመደና በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በአብዛኛው ራሱን የቻለ ህመም ሳይሆን ምልክት መሆኑን የሚጠቅሱት ባለሙያዎች፥ በጤና እክል ምክንያት ከሚፈጠር የህመም ስሜት ጋር ተያይዞ ራስ ምታት ሊከሰት እንደሚችልም ነው የሚናገሩት። በሰውነት ህዋሳት ውስጥ፣ በደም ቧምቧዎች፣ ነርቭና በሰውነት ውስጥ ያሉ ኬሚካሎችም በዚህ ጊዜ የሚከሰት የራስ ምታት ስሜት […]

ቃር

ቃር ወይንም በህክምና አጠራሩ /ኸርትበርን/ በመባል የሚታወቅ የህመም አይነት ሲሆን አብዛኞችን የሚያጠቃ እና እጅግ የተለመደም ችግር ነው።   በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት መሰማት በአብዛኛው ከምግብ በኋላ እና በእንቅልፍ ሰዓት የሚብስ ነው። ይህም የሚከሰተው የጨጓራ ውስጥ አሲድ ወደ ላይኛው የምግብ አስተላላፊ ቱቦ (ኢሶፋገስ) ሲገባ ነው። – ለቃር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች? * […]

ስክንድር ነጋና አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 746 ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋረጦ ነገ እንደሚለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ገለጸ።

አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጉርሜሳ አያና፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ጌቱ ጋሩማ፣ አቶ ተስፋዬ ሊበን እና አቶ በየነ ሩዳ ክሳቸው ተቋርጦ ዛሬ ተለቀዋል። ታራሚዎቹ እና ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ የተደረገው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ጉዳያቸው ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት እየታየ እንዲለቀቁ በወሰነው መሰረት ነው። ይቅርታ የሚደረግላቸው ሰው በመግደል፣ ከባድ […]

ንግስት ይርጋና ቴዎድሮስ ተላይ ከሚፈቱት መካከል አልተካተቱም

ንግስት ይርጋና ቴዎድሮስ ተላይ ከሚፈቱት መካከል አልተካተቱም በእነ ንግስት ይርጋ ክስ መዝገብ 1ኛ ተከሳሽ ንግስት ይርጋ እና 3ኛ ተከሳሽ ቴዎድሮስ ተላይ ብቻ ቀርበዋል። 2ኛ ተከሳሽ አለምነህ ዋሴ፣ 4ኛ ተከሳሽ አወቀ አባተ፣ 5ኛ ተከሳሽ በላይነህ አለምነህ እና 6ኛ ተከሳሽ ያሬድ ግርማ አልቀረቡም። በተመሳሳይ በእነ ኒሞና ጫሊ (በኦነግ ክስ የቀረበባቸው) ክስ መዝገብ […]

የእነ ንግስት ይርጋ መከላከያ ምስክርነት አከራከረ

~ ፍርድ ቤቱ የአማራ ክልል ባለስልጣናት በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ራሱ የሰጠውን ትዕዛዝ እንደገና እመረምራለሁ ብሏል በ2008 ዓም በአማራ ክልል በነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሰበብ የ”ሽብር” ክስ የተመሰረተባቸው እነ ንግስት ይርጋ ምስክርነት አከራክሯል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት እነ ንግስት ይርጋ ምስክርነት ለማሰማት ታህሳስ 12 /2010 ዓም በነበራቸው […]

በኦሮሚያ የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ እንደቀጠለ ነው

በኦሮሚያ ክልል የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል። ትላንት ያልተሳተፉ ከተሞች ዛሬ ተቀላቅለዋል። በጅማ ሁለት የሰላም ባስ አውቶቡሶች መቃጠላቸውን የደረሰን መረጃ ያስረዳል። በፍቼ የአጋዚ ወታደሮች በአንድ ትምህርት ቤት ላይ በወሰዱት ርምጃ አራት ተማሪዎች ክፉኛ ተጎድተዋል። በደብረዘይትና ጅማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ አደባባይ በመውጣት በስልጣን ላይ ያለውን […]

የኦፌኮ አመራሮች ከእስር ተለቀቁ

የኦፌኮ አመራሮች ከእስር ተለቀቁ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሰባት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/አመራሮች ከእስር ተለቀቁ። አመራሮቹ ከእስር እንዲለቀቁ የተደረጉት ክሳቸው ተቋርጦና በይቅርታ መሆኑን ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ገልጿል። ተከሳሾቹ ችሎት በመድፈር የተፈረደባቸው በመሆኑም ጉዳዩ ወደ ይቅርታ ቦርድ ሄዶ በሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር እንዲወሰን ከተደረገ በኋላ መለቀቃቸውን በሀገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የእነ […]