Month: February 2018

ንፅህናው ባልተጠበቀ ውሃ ውስጥ መዋኘት ለበሽታዎች ያለንን ተጋላጭነት ይጨምራል- ጥናት

ንፅህናው ባልተጠበቁ እንደ ባህር፣ ሀይቅ እና ኩሬ ያሉ ውሃዎች ውስጥ መዋኘት ለተለያ በሽታዎች በቀላሉ እንድንጋለጥ ያደርጋል አለ አዲስ የተሰራ ጥናት። ንፅህና በሌለው ውሃ ውስጥ መዋኘት ለሆድ ቁርጠት፣ የጆሮ ሕመምና ሌሎች በሽታዎች በቀላሉ እንደሚያጋልጥም ተመራማሪዎች ገልፀዋል። ተመራማሪዎቹ እንዳስታወቁት እንደ ባህር፣ ሀይቅ እና ኩሬ ያሉ ውሃዎች ውስጥ የሚዋኙ ሰዎች ለጆሮ ህመም በ77 […]

በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙ ኢንፌክሽኖች በጨቅላ እድሜ ወቅት በሚኖር የአንጎል እድገት ላይ ተፅእኖ አለው-ጥናት

በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥም ኢንፌክሽን ወይም የነብሰጡር እናቷን በሽታ የመከላከል አቅም የሚጎዳ ህመም በምትወልደው ህፃን የአንጎል እድገት ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ። በብራድልይ ፒተርሰን የሚመራው የሎስ አንጀለስ የልጆች ሆስፒታል የጥናት ቡዱን፥ በእርግዝና ወቅት በሽታን የመከላከል አቅም የሚያዳክም ኢንፌክሸን በህፃኑ አእምሮ ጤንነት ላይ የአጭር ወይም ረዥም ጊዜ አሉታዊ ተፅእኖን ያሳድራል። […]

በሽንት ናሙና አማካኝነት የሰውነታችንን ትክክለኛ ስነ- ህይወታዊ ዕድሜ ማወቅ ተቻለ

ተመራማሪዎች በሽንት ናሙና አማካኝነት በቀላሉ ከትውልድ ቀናችን ጀምሮ ከሚሰላው የእድሜ ቁጥር ይልቅ ስነ-ህይወታዊ የሆነውን ዕድሜን ማወቅ መቻሉን ገለፁ። በዚህ መንገድ ከእድሜ ጋር የተያያዙ በሽታዎችንና ሞትን የሚያስከትሉ ሁኔታዎችን መገመት እንደተቻለም አስታውቀዋል። ጆርናል ፍሮንቲየር እንዳተተው ከሆነ የሰዎች ዕድሜ ሲጨምር በሽንት ውስጥ የሚገኘው ኦክሲዳቲቭ የሚባለው ንጠረ ነገር ጉዳት እየጨመረ እንደሚሄድ ገልጸዋል። ከዚህ በመነሳትም […]

በተቃዉሞዉ 11 ሰወች ቆስለዋል አንድ ሰዉ ተገድሏል»አቶ ሙላቱ ገመቹ

የኦሮሞ ፌዴራሊስ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲናን ጨምሮ ከእስር የተፈቱ የፓርቲዉ አመራሮች ከነቀምት ከተማ ህዝብ በተደረገላቸዉ «የእንኳን ደስ ያላችሁ» ጥሪ መሰረት ባለፈዉ እሁድ ወደ ቦታዉ አምርተዉ ነበር። ይሁን እንጅ ከቦታዉ ሊደርሱ ጥቂት ኪሎሜትሮች ሲቀራቸዉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ወደ ከተማዉ እንዳይገቡ በጸጥታ ሀይሎች መከልከላቸዉን የፓርቲዉ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ […]

መድረክ አስቸኳይ የድርድር መድረክ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀረበ

በሥልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መራሹ መንግሥት ኢትዮጵያን ከገባችበት የፖለቲካ ቀውስ የመታደግ ብቃት የለውም ያለው ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)፣ ኢሕአዴግን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በአስቸኳይ ተገናኝተው የሚነጋገሩበትና የሚደራደሩበት መድረክ እንዲፈጠር ጥሪ አቀረበ፡፡ መድረክ ይህን ጥሪ ያቀረበው፣ ‹‹ኢሕአዴግ አገራችንን ካስገባት ቀውስ ውስጥ የማስወጣት ብቃት አይኖረውም›› […]

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኃላፊነታቸው ተሰናብተውም ሙሉ ደመወዝና አበላቸው አይቋረጥም

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኃላፊነታቸው ተሰናብተውም ሙሉ ደመወዝና አበላቸው አይቋረጥም እየተጋጋለ የመጣውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ «የመፍትሔው አካል መሆን አለብኝ» በሚል ራሳቸውን ከገዥው ፓርቲ ሊቀመንበርነት እና ከአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያሰናበቱት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተገቢው ጥቅማ ጥቅማቸው የሚከበርላቸው መሆኑን ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የሕግ ባለሙያዎች ጠቆሙ። ከኃላፊነት የተነሱ የሀገርና የመንግሥት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ […]

ፓርላማው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ እንዲወስን በአስቸኳይ ተጠራ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአስቸኳይ አዋጁ ላይ እንዲወስኑ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠሩ፡፡ ከየካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ወር ዕረፍት የወጡት የፓርላማ አባላት ለአስቸኳይ ስብሰባ በመጠራታቸው ምክንያት፣ ከማክሰኞ የካቲት 20 ቀን 2010 ጠዋት ጀምሮ ሪፖርት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የፓርላማው አባላቱ የተጠሩት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የካቲት 9 ቀን 2010 […]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያስገነባው ያለው ባለ 373 ክፍሎች ሆቴል ሰኔ ላይ ይጠናቀቃል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያስገነባው ያለው ባለ 373 ክፍሎች ሆቴል ሰኔ ላይ ይጠናቀቃል ተባለ፡፡ ሁለተኛው ፌዝ ባለ አንድ ሺህ ክፍል ለመገንባት እቅድ ተይዟል። እየተገነባ ያለው ባለ 373 ክፍሎች ሆቴል ነው፡፡ በሰኔ ወር ግንባታው ይጠናቀቃልም ብለዋል፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ ከራሱ ደንበኞች በተጨማሪ ለሌሎች የሆቴል አገለግሎት ፈላጊዎች ክፍት በማድረግ በሀገር ውስጥ ያለውን የሆቴል እጥረት […]

ብአዴን አመራር አምላኪ ድርጅት አይደለም!” የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን

የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ማዕከላዊ ኮሚቴው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ዙሪያ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ረጅም ጊዜ በመውሰድ በዝርዝር የተመለከታቸው ሃገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች በዝርዝር ተፈፃሚ እንደሚሆኑ አብራርተዋል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ ከተናገሩት ጭብጦች መካከል፡- “ለውጥ መጀመር በራሱ ጥሩ እርምጃ ነው፤ ለውጥን ማስቀጠል ግን ትልቅ […]

ኤኤንሲ ያለ ካሳ የነጮችን መሬት የመንጠቅ ሃሳብን እንደሚደግፍ አስታወቀ

የደቡብ አፍሪካው ገዥ ፓርቲ ኤኤንሲ በነጮች የተያዘን መሬት ያለካሳ መውሰድን በሚመለከተ ፅንፈኛው ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ ፓርቲ ያቀረበውን ሃሳብ እንደሚደግፍ አስታውቋል። ከትናንት በስቲያ ጉዳዩን በሚመለከት በፓርላማ የተደረገውን ክርክር ሲመሩ የነበሩት የኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ ፓርቲ መሪ ጁሊየስ ማሌማ ነበሩ። “የእርቅ ጊዜ አብቅቷል። አሁን ጊዜው የፍትህ ነው። የነጮች መሬት ተወስዶ ለፍትሃዊ ክፍፍል መቅረብ […]