ገንዘቧን አፍሳ ህልሟ ያልተሳካላት ወጣት

ህልሟ ተሳክቶ አንጀሊና ጆሊን ለመምሰል ሞክራ በተቃራኒው አንጀሊና ጂኒን ለመምሰል በቅታለች

(ፀሀፊ፦ደረጀ ኤልያስ አለሙ) ይህን ምስል ያገኘሁት ከ internet ሲሆን ታሪኩም የአንዲት የታዋቂዋ አክትረስ angelina jolle አድናቂ ወጣት መጨረሻን ያትታል እናም ይህች ወጣት አክትረሷን ለመምሰል ባደረገችው ተደጋጋሚ የፊት ቀዶ ጥገና (plastic surgery)
ህልሟ ተሳክቶ አንጀሊና ጆሊን ለመምሰል ሞክራ በተቃራኒው አንጀሊና ጂኒን ለመምሰል በቅታለች እናም ለዚህ የጥፋት ስኬቷ የእንኳን ደስ ያለሽ መልእክታችንን እያደረስን
ያው ሰው የእጁን ስራ ፍሬ ይበላል ይላልና መፅሀፉ) ለዛሬ ግን እኛን ወጣቶችን ስሚመለከተን ከተመሳሳይ ስህተቶች ለመዳን ለጥንቃቄ ይረዳን ዘንዳ ትንሽ እናውራ ።

እኔ የዚህ ታሪክ ተያቢ ወንድማችሁ በስሱም ቢሆን የዚህ ጉዳይ ተጠቂ ነኝ ብዬ ስለማምን ከታሪኬ ተማሩ
ብዬ ይችን ከትቤያለሁ ነገሩ እንዲህ ነው የሆነው ሀይስኩል ተማሪ ሆኜ የሆነች እዚህ ግቢ የማትባል የሰፈሬን ልጅ አፍቅሬ ነበር (ልብ በሉ ንዴቴ በሷ ላይ አይደለም በራሴ ላይ ነው !!

እሚገርማችሁ አሁን መንገድ ላይ ሳገኛት እንኳን ሰላምታ የለንም በጊዜውም ምንም አይነት የፍቅር ግንኙነት አልነበረንም
ታዲያ ፈርዶብኝ በቀነ ጎደሎ ወደድኳትና ፎቶዋን ክንዴና ደረቴ ላይ ካልተነቀስኩ ሞቼ
እገኛለሁ ብዬ ቀወጥኩት በመጨረሻም ስሟንና በጦር የተወጋ ልብ ምስል ደረቴ ላይ ተነቀስኩ
(ምን ያስቃችኋል ይሄኮ የአብዛኛው ኢትዮጽያዊ ወጣት ታሪክ ነው ደግሞም እኔ በግዜው እንደእናንተ ነገን የሚያይ ጓደኛም ሆነ መካሪ ወንድም አላገኘሁም)

በሰራሁት ስህተት መፀፀት ለመጀመር ስድስት ወር አልቆየሁም ስሟን ለማጥፋት ሙከራ ማድረግ ስጀምር ይሄው ታዲያ በዚህ ንቅሳት እና ለማጥፋት በተደረገው ሙከራ ደረቴ ተቦጫጭሮ እረኛዋ ከነብር ያስጣላት የበግ ግልገል መስያለሁ ይኸው እስከ አሁን ሰው ፊት ልብሴን ማውለቅ አፍራለሁ ጠባሳውንም ባየሁ ቁጥር የሚሰማኝ የልብ ቁስለት ተዉት ያማል !!

በቃ ያማል በጣም በተለይ ምን ሆነህ ነው ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠት ያማል !!! የእውነት ያማል !!

የፈጠራ ታሪክ ሁሉ ታዘጋጃለህ እናም ወንድሜ በምታደንቀው/በምትወደው ሰው ምክንያት ሰውነትህ ወይም አስተሳሰብህ ላይ የምታደርገው ለውጥ ቋሚ ጠባሳ አይኑረው ነገ ልትጠላው ወይም ማየት ላትፈልገው ትችላለህ የለውጥ ህግ ከተፈጥሮ ህጎች አንዱ ነው እድገትም እንደዛው ከፈለክ በቀላሉ የሚስተካከሉ የፀጉር ስታይል ወይም ተለጣፊ ስቲከር ታቱ ብትጠቀም ችግር አይኖረውም ቋሚ ነገሮችን ግን እንዳትሞክረው እኔን አይተህ ተቀጣ ።

ታዲያ ወንድሜ እልሀለው !! ጥላህ ልትሄድ ለምትችል ኮረዳ አብሮህ የሚኖር የገዛ ክንድህን አትጉዳ አእምሮህን ስሜትህን አትጉዳ (አይ ግጥም !!)

አንቺም እህቴ እልሻለሁ !! በሌላ ሊቀይርሽ ለሚችል ጎረምሳ በሀዘን ፍላፃ ልብሽ አይበሳ የወደፊት ህልምሽ አይረሳ (ግጥሙን ደገምኩት !!)
በተረፈ ይሄን ፅሁፍ ካነበብክ በኋላ ከፈለክ ሻሩክን ከፈለክ ሽሬክን ለመምሰል plastic surgery
መሰራት ወይም ሶስተኛ ክፍል ደጋግመህ የወደቅክበትን የትምህርት ቤት ካርድህን መነቀስ መብትህ/ሽ ነው አያገባኝም ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *