ትረምፕ የአሜሪካን ኤምባሲ ወደ እየሩሳሌም ሊያዛውሩ ነው ተባለ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ እየሩሳሌም ለማዘዋወር መወሰናቸውን ተናገሩ።

ፕሬዝዳንቱ ውሳኔያቸውን ለዮርዳኖሱ ንጉስ አብደላ እንደነገሯቸው የዮርዳኖስ ቤተ-መንግሥት ያወጣው መግለጫ ይጠቁማል።

ንጉስ አብደላ እርምጃው ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት የከፋ ዳፋ እናደሚያስከትል መናገራቸውን መግለጫው ጨምሮ አትቷል።

ዓለም አቀፍ መሪዎች የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አወዛጋቢ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን እንደ እስራኤል ዋና ከተማ ካወቁ እና የሀገራቸውንም ኤምባሲ ከቴል አቪቭ ወደዚችው ከተማ ካዛወሩ ሙስሊሞችን ሊያስቆጡ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም ለማውረድ የተጀመረውን ጥረት ሊጎዱ ይችላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋቸው ነበር።

እስራኤል እና ፍልስጤማውያን እንደ ዋና ከተማቸው የሚመለከቱዋት የኢየሩሳሌም ጉዳይ ሁለቱን ወገኖች አሁንም እያወዛገቡ ካሉት ጥያቄዎች መካከል ዋነኛው ነው።

አሜሪካዊው ፕሬዚደንት የኢየሩሳሌምን ወቅታዊ አቋም የሚቀይር ርምጃ እንዳይወስዱ ፍልስጤማውያን እና የዐረብ ሊግ ሲያስጠነቅቁ፣ ቱርክም ከዩኤስ አሜሪካ ጋር ዲፕሎማቲክ ግንኙነቷል ልትቋርጥ እንደምትችል ዝታለች።

ዩኤስ አሜሪካ ይህን ውሳኔ ከመውሰዷ በፊት ጉዳዩን በሚገባ እንድታጤነው ካስጠነቀቁት መካከል የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዚግማር ጋብርየል ይገኙባቸዋል።

ይህ ዓይነት ርምጃ ምን ዓይነት ከፍተኛ መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል ሁላችንም እናውቀዋለን።

በዚህ ጥያቄ ላይ ጀርመን የያዘችው አቋም አይቀየርም።
የኢየሩሳሌም ጥያቄ መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለው በሁለቱ ወገኖች መካከል በሚደረግ ቀጥተኛ ድርድር ብቻ ነው።
ሌላው ቀውሱን ሊያባብስ የሚችል ርምጃ ሁሉ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። »

source dw amharic

 

ትረምፕ የአሜሪካን ኤምባሲ ወደ እየሩሳሌም ሊያዛውሩ ነው ተባለ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *