የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ጀመረ

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ። ምክር ቤቱ የክልሉ የ2010 በጀት ዓመት የ9 ወራት የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ሪፖርትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። ከዚህ ባለፈም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ6 ወራት ሪፖርት እና የ2009/2010 በጀት ዓመት የተከናወኑ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን አድምጦ በመገምገም እንደሚያጸድቅም […]

ሩሲያ የኢትዮጵያን የባህል ልማት እንደምትደግፍ ገለፀች

አዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ያዘጋጁት 120ኛ ኢትዮ-ሩሲያ ዲፕሎማሲ ግንኙነት የሚዘክር የፎቶ ኤግዚብሽን ዛሬ ሚያዚያ 15 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከፈተ። በኢትዮጵያ የሩሲያ-አምባሳደር ሴቬሎድ ቲኬቼንኮ በመክፈቻ ንግግራቸው ሩሲያ የኢትዮጵያን የባህል ልማት እንደምትደግፍ አስታወቀዋል። ከአዲስ አባበ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በመስኩ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ነጻ የትምህርት […]

ያችን ምሽት! – ዶ/ር ደመላሽ ገዛኸኝ

በዚያች ሌሊት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ውስጥ ተረኛ ነበርኩ። የእለቱ ተረኛ ነርሶች “ሪፈራል ከሐዋሳ ተልኮልናል፤ ይስማዕከ ወርቁ የመኪና አደጋ ገጥሞት መጥቷል!” ብለው እንደነገሩኝ ፡ ከሌሎች አጋሮቼ ጋር ተባብረን አስፈላጊውን የድንገተኛ ህክምና አደረግንለት። ከቤተሰቦቹ ጋር ፡ እጅጉን የምወደው አርቲስት ሽመልስ አበራ (ጆሮ) እጅጉን ተጨንቆ ስለሁኔታው ሲጠይቀን ነበር። ሁኔታውን አስረድተን ፡ […]

የአሜሪካ መንግስት ልዑካን ወደ አስመራ አቀ

የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ምክትል ሀላፊ ዶናልድ ያማማቶ የተመራ የአሜሪካ የልዑካን ቡድን ወደ ኤርትራ አቀና። የልዑካን ቡድኑ ከስኞ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በአስመራ በሚኖረው ቆይታ ከሀገሪቱ ባለስልጣናትና በአስመራ ተቀማጭ ከሆኑ የዲፕሎማቲክ ማህበረስብ አባላት ጋር ይነጋገራል። የልዑካን ቡድኑ ተልዕኮውን በይፋ አላሳወቀም። የጉብኝቱ ዋና ተልዕኮ በኤርትራ መንግስት ተይዘው ለእስር የተዳረጉ የአሜሪካ ኤምባሲ ስራተኞች ጉዳይ […]

ገዢው ፓርቲ፤ “ከአገርህ? ከሥልጣንህ?” ተብሎ ይጠየቅልን ( ኤልያስ )

ለወጣቶች ከተመደበው 10 ቢ.ብር ውስጥ 4 ቢ.ብር ሥራ ላይ አልዋለም •ኢህአዴግ በኛ ጉዳይ፣ ከኛ ተደብቆ ይወስናል!! • ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የምናተርፈውን በግልጽ እንወቀው በርግጥ ዛሬ ያመጣው አመል አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ነፍሴ ሁሌም እንዲሁ ነው! ላለፉት 27 ዓመታት የኖረበት ዘዬው ነው፡፡ በቃ ድብቅ ፓርቲ ነው – ምስጢረኛ! ድብቅነት ባህሉ ነው፡፡ ስብሰባውና ግምገማው […]

የኤርትራ ወታደሮች በሁመራ በኩል ገብተው 14 ኢትዮጵያውያንን አፍነው መውሰዳቸውን አረና ፓርቲ አስታወቀ

ኤርትራ ወታደሮች ድንበር ጥሰው በመግባት 14 ኢትዮጵያውያንን አፍነው መውሰዳቸውን የአረና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረሥላሴ ገለጸ:: “ሻዕብያ 14 ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ኣግቶ ወሰደ” በሚል ርዕስ አቶ አምዶም በሰበር ዜና በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በመግባት 14 ወጣቶችን አግተው የወሰዱት በሑመራ ኣከባቢ ልዩ ሱሙ ዲማ ከተባለ ቦታ […]

ለሱስ ማገገሚያ በየዓመቱ ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ይደረጋል›› – ባህሩ ዘውዴ

ጫት ካቲን፣ ካቲኖልና ሜታካቲን የሚባሉ አነቃቂ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ይይዛል›› አደገኛ መድኃኒቶችን፣ አደንዛዥ እፆች ምንነታቸው እና ለመቆጣጠር የወጡ ዓለም አቀፍና የሀገራችን ህጎች ምን ይመስላሉ፤ በአለምአቀፍ ደረጃ በህገወጥ መንገድ የሚዘዋወሩት መድሃኒቶችና አደንዛዥ እፆች 400-ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይገመታል፡፡ ከነዚህ የሚገኙት ገቢዎችም ለተለያዩ ወንጀሎች፣ የፖለቲካ ጫናዎችና ለሽብር ድጋፍ ይውላሉ፡፡ የመንግስት በጀት ለልማት ሳይሆን […]

ከህክምና ሙያ ላይ እጃችሁን አንሱ” – ዶ/ር አብርሃም አማረ

የከበረውን በማዋረድ ዉርደት እንጂ ክብር አይገኝም ” ሚሊዬኖች ይድናሉ ትቂቶቹ ግን ሊሞቱ ይችላሉ ፡፡ አይደለም መድሃኒት ውጠህ ውሃም ጠጥተህ ትን ብሎህ ልትሞት ትችላለህ፡፡ ብቁ ያልሆኑ መድሃኒቶች ሀገሪቷን እንደወረርሽኝ በተቆጣጠሩበት ዘመን መንግሥትም ይሁን መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኮንትሮባንድም ይሁን በሌላ መንገድ ማንነታቸው ያልታወቁ መድሃኒቶችን ለዜግቹ እየቸበቸበ ባለበት ሀገር ( ለዚህም ማሳያዉ ባለፈው […]

አስደናቂ የፓፓዬ የጤና ጥቅሞች!

ፓፓዬ በቫይታሚን ሲ እጅግ የበለፀገ የዓለማችን የፍራፍሬ አይነት ነው። ፓፓዬ ካሉት በርካታ የጤና በረከቶች እነሆ የተወሰኑትን እንካችሁ 1.በሰውነታችን የኮሌስትሮል መጠን እንዲቀንስ የጎላ አስተዋኦ ያበረክታል! ፓፓዬ በፋይበር፣ ቫይታሚን ሲ እና የተለያዩ አንቲኦክሲዳንቶች የበለፀገ በመሆኑ እነዚህ ነገሮች በደምስሮቻችን ውስጥ የኮሌስትሮል ክምችት እንዳይኖር ያደርጋሉ። በዚህም የስትሮክ ህመም እና ሀይፐርቴንሽን ችግር እናዳይገጥመን የጎላ ሚና […]

ቶንሲል ህመም ለኩላሊት መድከም ለልብ ህመምና ለሞት ሊዳርግ ይችላል

የቀዘቀዘ ምግብን ወይም መጠጥን አብዝቶ መጠቀም አሊያም በሃይለኛ የፀሐይ ሙቀት በመመታት ይከሰታል ተብሎ በአብዛኛው ህብረተሰብ ዘንድ የሚታሰበው የቶንሲል ህመም መነሻ ምክንያቱ ከእዚህ በእጅጉ የተለየና ተገቢውን ህክምና በወቅቱ ካላገኘም እስከሞት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት የሚያስከትል አደገኛ የጤና ችግር ነው፡፡ ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች በፀሐይ ላይ መመገብ፣ እንደ አይስክሬም ያሉ የቀዘቀዙ ምግቦችን በተለይ ለህፃናት […]